TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1818 713
AB PHOTOGRAPHU & GRAPHIC DESIGN

#አትፍረድ

በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ መፍረዱን የሚገባው ከእኛ ይልቅ ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡

እርሱ እግዚአብሔር ብቻ የማንኛችንም ግልፅና ሥውር ነገሮችን ያውቃልና እሱ ብቻውን በማንኛቸውም ነገሮችና በማናችንም ላይ የመፍረድ ስልጣን አለው፡፡

እግዚአብሔር የማንኛውንም ሰው ዝንባሌ ችሎታ አካላዊ ሁኔታ ክህሎት ያውቃል፡፡ ስለዚህ በሚፈርድበት ጊዜ በእውነት ይፈርዳል፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ "አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል" በማለት ይህን የእግዚአብሔርን ስልጣን እንድንረዳ ያሳሰበው፡፡

በሌሎች የሚፈርዱ ሰዎች መርዙን እንደሚተፋ እባብ ናቸው፡፡ በሌሎች መፍረድ የደረሰበትን ሁሉ እንደሚገድል መርዝ ነው፡፡
አንድ ሰው ኃጢያት ሲሰራ ብታገኘው አትሳለቅበት አትናቀውም አንተም በጠላቶችህ እጅ እንዳትወድቅ፡፡

ወንድምህን በደሉን የማትሸፍን ከሆነ ቢያንስ አትፍረድበት ፡፡
ባልንጀራህ በበደለ ጊዜ ለአንተ እንደምታለቅስለ እዘንለት ምክንያቱም ሁላችንም ለውድቀት የተጋለጥን ነንና፡፡ በዚህም መንገድ እርሱን በጭካኔ ፍርድ ሳይሆን በርህራሔ ፍቅር ቅረበው፡፡ በውድቀት ውስጥ ቢገኘም እንኳ ባልንጀራህና ወንድምህ ነውና፡፡ ሐጢያቱን ውሰድ ያ ለራስህ እንደሆነ አድርገህ ግለፅ ስለእርሱም ሙት፡፡

እግዚአብሔር በፍቅሩና በርሕራሔው ድንቅ ነው፡፡ ሁሉንም ሊያደርግብን መብት ያለው የሚችልም ቢሆን እንኳን እርሱ ይቅር ይላል፡፡ በማንም ለመፍረድ መብቱ የሌለን እኛ ታዲያ ለምን ይቅርታን አናደርግም???

በልቡ ለሌላው ላይ የሚፈርድና አፉንም በርሱ ላይ የከፈተ በወንድሙ ላይ በፈረደበት ሀጢያት እርሱም ይወድቅበታል መለኮታዊ ጥበቃው እርሱ ላይ ስለፈራጅነቱ ይለየዋል፡፡

አንድ ሰው ዛሬ ሀጢያት ሲሰራ ብታየው አትፍረድበት ሀጢያቱን በሰራበት ቀን ማታውኑ ንስሐ ገብቶ እግዚአብሔር ይቅር ብሎት እንደሆነ በምን ታውቃለህ??

ቅዱስ ዮሐንስ ዘአሲዩት በአንድ ወቅት ይህን ተጠየቀ:-በክፉ ላይ የሚፈርድ ሰው ክፋትን ይጠላልን??

"አይጠላም ሁሉም ሰው ክፉን እፀየፋለሁ ይላል ክፋትን እንደምንፀየፍ ሊመሰክርልን የሚችለው ግን #ስራችን ብቻ ነው፡፡"

በእርግጥ በሌሎች የመፍረዳችንአላማ ምንድነው??

ያንን ሰው ሰዎች እንዲጠሉት ትሻለህን? ወይስ እግዚአብሔር እንዲያጠፋውና እንደክፉ ስራው እንዲቀጣው ትፈልጋለህ??

ቅዱስ ኤሪስ እንዲህ ይላል:- አንድ ሰው በሐሜት የወንድሙን ሥጋ ከመብላት የወንድሙን ደም ከመጠጣት ይልቅ ስጋ ቢበላ ወይንም ቢጠጣ ይሻላል፡፡ እባብ በወሬው ለሔዋን ከገነት መጥፋት(መሰደድ) ምክንያት እንደሆነ ሁሉ ወንድሙንም የሚያማ እንዲሁ ነው፡፡ እባብ ከእርግማኑ እንዳላመለጠ የዚህም ሰው የራሱ ነፍስ ከጥፋት አያመልጥም፡፡

በራስ መፍረድ ግን ወደ ትህትና እና ንፅህና የሚያደርስ የትሩፋት የዕድቅ ስራ ነው፡፡
ቅዱስ መቃሪዮስ:- "ወንድሜ ሆዮ ሳይፈረድብህ በፊት በራስህ ፍረድ" እንዳለ ተገቢ ፍርድን የመቀበል ሁኔታ ነው፡፡

እኛ በራሳችን ላይ ብንፈርድ ፈራጃችን በእኛ ይደሰታል እንዲሁም ራሱን ለማስተካከል ራሲን የሚገስፅና በራሱም ላይ የሚፈርድ ያ ሰው በሌሎች ላይ ለመፍረድ የሚያነሳሳ ውስጣዊ ማንነት አይኖረውም ምክንያቱም እንደሌሎች ምናልባት ከእነርሱ በባሰ የሀጢያተኘነት ስሜት አድሮበታልና፡፡

በራስ መፍረድ ሰውን በሌሎች ከመፍረድ ይጠብቀዋል፡፡

ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ደግሞ:- " ስለራሱ ሀጢያት የሚጨነቅ ማንም ስለሌሎች ሀጢያት የሚናገርበት ጊዜ እስከሚያጣ ወደ ራሱ ልብ እንደሚገባ ሲናገር የራሱን የሞተ ዘመድ ትቶ ስለባልንጀራው(ጎረቤቱ) የሞተ ዘመድ ሊያለቅስ የሚሔድ እሱ ማነው" ይለናል፡፡

#አትፍረድ:- አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ
ትርጉም:- ዲ/ን ማለደ ዋስይሁን

ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንዳቀረብኩት መፅሐፉ ላይ የአባቶችን አባባል ነው የሚጠቀሙት እኔ አብዛኛውን ስማቸውን ሳልጠቅስ አያይዤ ነቅ ያቀረብኩት ወጥነት እንዲኖረው ብይ በማሰብ ነው፡፡

@jahABP ነኘ 😊🙏😍 አስተያየታችሁን አድርሱኘ

"እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኀልና በምትሰፍሩበትም መሥፈሪያ ይሰፈርባችኀልና፡፡" ማቴ ፪-፩(2-1)

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →