TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1702 1.18K
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

"አንተ ቤትህን ትሰራለህ መቃብርህን ደግሞ
ሌላ #ሰው ይሰራል"


አንድ ቀን ጀርመን ተማሪ ሳለሁ ርቦኘ በአንድ ሆቴል ደጃፍ ተሰለፍኩ፡፡ እዚያ ሀገር ወደምግብ ቤት ሄደህ ትሰለፍና ከውስጥ ተመጋቢው ጨርሶ ቦታውን ሲለቅ በተራህ ትገባና ቦታህን ይዘህ ትበላለህ፡፡

ታዲያ የኔ ተራ ታዲያ ደረሰና ገብቼ አንድ ወፍራም ጀርመናዊ የተቀመጠበትን ጠረቤዛ ላይ ሄጄ ከፊት ለፊቱ ተቀመጥኩ፡፡ እሱ እየተመገበ ነበር እኔም አዝዤ ስመገብ በድንገት ተመለከትኘና ደነገጠ😳😳😱፡፡

"ከየት ነው የመጣኸው?" አለኘ፡፡

"ከኢትዮጽያ..." አልኩት፡፡

"ኦ! በረኻብ ትሰቃያላችሁ፡፡ ይኸው እኔም ከደሞዜ በየወሩ 25 ማርክ አዋጣለሁ...አለኘ፡፡

የነበረኘ አማራጭ ሀቁን ማስረዳት ነው፡፡ የረሃባችን በለው የችግራችን የመታረዛችን...እውነተኛው ምክንያት ጦርነት ነው፡፡ ጦርነት ከየት መጣ ብትለኘ ከነጮች እልሃለሁ፡፡ እኛ በሠራነው መሳሪያ ስንጫረስ አይተህ ታውቃለህ? ለመኖር የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ከዚህች እግዜር ከባረካት አህጉር ይወስዱና በምትኩ የጦር መሳሪያ ይሰጡናል፡፡ በዚያ ደግሞ እኛ እንጫረሳለን፡፡

ወደ ታሪኩ ልመልስህና ይህን ጀርመናዊ ነጭ ቢያንስ ሀቁን ማሳየት እንደሚገባኘ አመንኩበት፡- "ጌታዬ! ቡና ትጠጣለህ..." አልኩት፡፡

"አዎን እጠጣለሁ" በማለት መለሰልኘ፡፡

"በቀን ስንት ሲኒ ቡና ትጠጣለህ?" አልኩት፡፡ በትንሹ አራት ሲኒ ቡና እንደሚጠጣ ነገረኘ፡፡

"በቀን አራት ሲኒ ቡና ከጠጣህ በወር 120 ሲኒ ቡና ትጠጣለህ ማለት ነው....ይህ ደግሞ በወር 150 ማርክ ታወጣለህ ማለት ነው፡፡ ለመሆኑ ቡና ከየት እንደሚመጣ ታውቃለህ? ኮኮዋ ከየት እንደሚመጣ ታውቃለህ? በየቀኑ የምትገጥመው በየአይነቱ ከአንድሺህ በላይ የሆነ ኬክና ክሬም መስሪያ ኮኮዋ ከየት እንደሚመጣ ታውቃለህ? ብዬ ጠየኩት አያውቅም!

"አንተ 25 ማርክ ለሀገሬ በመላክ ትመፃደቃለህ ነገር ግን ቢያንስ ሀገሬ ለአንተ በወር የ150 ማርክ ቡና ታጠጣሃለች ለእሷስ የሚገባትን ክፍያ ሰጥታችኀታል? ....የምትጠጣው ቡና የሚመጣው ከኢትዮጵያ ነው....መገኛዋም ኢትዮጽያ ነው....፡፡ የምትገምጠው ኬክ የሚሰራበት የካካዋ ፍሬ የሚመጣው ከአህጉሬ ከጋና አይቮሪኮስት ነው...."

በመደነቅ ይሰማኘ ነበር፡- "ለአንተ የእኔ ሀገርና አህጉር ውሃ የሌላት ደረቅ መስላ ትታይሃለች እንኳን የእኔ ሀገር አይደለችም ሰሃራ በረሃን ብትቆፍረው እንኳን ውሃ ይወጣዋል፡፡ ነገር ግን እናንተም የምትሰጡት ውሃ የምናወጣበትን ቴክኖሎጂ ሳይሆን የምንጫረስበትን ታንክ ነው...እናም ለረሃባችን ለችግራችን ምክንያቱ ማን እንደሆነ ገባህ?" በሰማው ተደንቆ እንዳፈጠጠብኘ ተሰናብቼው ሄድኩ፡፡

በስራዬ ውስጥ ሻርክ አለ አዞዎች አሉ ፈረስ አለ እነዚህ የምጠቀመው ተነፃፃሪ የሆነን ገፅታ ለማሳየት ነው፡፡ ሰው ያልሆነን ሰው የምትገልጥበት መንገድ አለህ እንደአንበሳ የሆነን ሰውም በራስህ መንገድ ታስቀምጠቃለህ እነንደፈረስ የሆነ ሰው ደግሞ አለ( ፈረስ በነገርህ ላይ የእኔ ባህሪይ ነው!) ፈረስ እጅግ ታጋሽ ነው ስለፈረስ ባህሪይ ካወቅህ እስኪመረው ድረስ ሰፊ የመታገስ ችሎታ ያለው እንስሳ ነው፡፡ ያስመረርከው ቀን ግን አንተኝ አያድርገኘ!

እናም በስዕሌ ውስጥ የምነጠቀምባቸው ተምሳሌቶች እነዚህና እነዚህ ሲመስሉ በዋነኘነት ግን ፈረስ እናት ሕፃን ፀሀይን አበዛለሁ፡፡
ይህ ደግሞ ያለምክንያት አይደለም፡፡

#ሕፃን_ሰለወደፊቱ_ይነግርሃል፡፡

ልጅ መውለድ ሳይሆን አባት መሆንመ ትልቅጨቁም ነገር ነው፡፡ እሱን መንከባከብና ማሳደግ በተለይ ማስተማርም ያስፈልጋል፡፡ በእሱ እውቀት፡ላየ የወደፊቱን ትውልድ መገንባትህን ታረጋግጣለህ፡፡ እናት ደግሞ ህይወት ሰጪ ነች፡፡

ጦርነቱም ረሃቡም ድርቁም ሲመጣ የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ እናትና ህፃናት ናቸው፡፡

#ፈረስ_የአፍሪካ_ህዝብ_ነው፡፡
ቻይ ሕዝብ ማለት ነው፡፡ ይህ ቻይነቱ ግን እስኪመረው ድረስ መሆኑንም በዚያው መልዕክት አስተላልፌበታለሁ ፡፡

#ፀሀይ_ደግሞ_ውበት_ናት፡፡

ጀርመን እኮ ልብስህን አጥበህ በ15 ቀንም አይደርቅም፡፡ ይችህን የመሰለች መድኃኒት የሆነች ፀሀይ እንደልብ የምትወጣበት አህጉር ግን ለእኛ እንደምንም እንቆጥራታለን፡፡

እዚህ ዋጋ ስለማንከፍልባት አይሰማንም እንጂ የፀሀይን ኃይል ብቻ በመጠቀም ብዙ ነገር መስራት በቻልን ነበር፡፡

አእምሮ ባርነትና እውቀት ማጣት በእኛ በአፍሪካዊያን ላይ እየተጫወተብን ነው፡፡ ለዚህም ነው መከራችንን የመብዛቱ እያልኩ የምገኘ፡፡ አንድ እውነት መናገር ግን ይገባኛል፡፡ በእኛ በጥቁር ህዝቦች ላይ የሚፈፀመው ግፍ ሁሉ ጊዜያዊ ነው፡፡ ዛሬ በክፋት ሊያጠቃህ ይመጣ ይሆናል ተመልሶ ሲመጣ ግን ቆመህ አትቆየውም፡፡

#የአፍሪካም_ተስፋ_እንዲሁ_አንድ_ቀን_እንደሚያንሰራራ_አምናለሁ፡፡

ስዕሎቼ ውስጥ አንዳንዴ የማስቀምጣቸው የራሴንም ስሜት መሆኑን ተረዳ እኔ አጠገቤ ሌላው በረሃብ ሲቃጠል እያደረ ሰላም የማገኘ ይመስልሃል??

የእንቁራሪቷ ምን አለች መሰለህ፡-
"ኧረ የሰው ቤት እየተቃጠለ ነው፡፡ በማለት ትጮኻለች አሉ፡፡

ጓደኛዋም "ታዲያ የሰው ቤት ቢቃጠል አንቺ ም# ያስጮህሻል እኛ ያለነው ውሃ ውስጥ!" ትላለች፡፡

እንቁራሪቷ ምን ብላ መለሰችላት መሰለህ መሰለህ፡-
"ሞኞ! እሳቱን ለማጥፋት እኮ ውሃ የሚወስዱት ከዚህ ነው፡፡ #አንድም_ከባሊ_ጋር_መሔድ_አለ_አሊያም_ደግሞ_ነገ_ውሃው_ይደርቃል፡፡"

በተለይ በተለይ በአፍሪካ ከቅኘ ግዛት ጊዜ ጀምሮ በታሪክ ውስጥ የመጣብን ጉዞ አሁን እያባላን እያጨፋጨፈን ይገኛል፡፡ ስለዚህም ሥራዎቼ በዋነኘነት አፍሪካዊያን የዚህን ችግራቸውን ምንጭ መለስ ብለው እንዲመረምሩት የሚጋብዙ ናቸው፡፡

ይሉናል ሰዓሊና ቀራፂ #ጌታቸው_ዮሴፍ(ረዳት ፕሮፌሰር)
አቦ እኚህን ገራሚ #ሰው ያሉትን አንብማ የነፍ እውቀት ነው የምትገበዩት፡፡ አብሶ በኢትዮጵያዊነት በአፍሪካነታቹ ምትኮሩ በሙሉ💪💪💪😍😍😍፡፡
ሰዓሊያን ካላቹ የእውነት አያሌ ምክር እና እውቀት ትገበያላቹ ይነበብ ይነበብ....👏👏👏


የመፅሐፍ ርዕስ #ሰው

#ከኃይለጊዮርጊስ_ማሞ( ጲላጦስ)

@jahABP ነኘ ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንዲህ ቀንጭቤ አቀረብኩላቹ ሌላ ጊዜም እንቀጥለዋለን.......
ሙሉውን እንድታነቡ ጋበዝኳቹ፡፡
ለፀሀፊው ከፍ ያለ ፍቅርና አክብሮቴን ለመግለዕ እወዳለሁ፡፡

እንኮራለን በአፍሪካዊታችን በኢትዮፕያዊነታችን እንኮራለን😍😍😍😍💪💪💪💪💪

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →