TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1701 1.1K
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#አደገኛ_ነው

"ኃጢያት የመንገድ እነቅፋት ሊሆን ይችላል የሕይወት ግብ ከሆነ ግን አደገኛ ነው፡፡
ቁሳቁስ ስኬት ሊሆን ይችላል ሕይወት ከሆነ አደገኛ ነው፡፡
ወዳጆች የሚያስደስቱ ሊሆኑ ይችላሉ እግዚአብሔርን የሚተኩ ከሆነ ግን አደገኛ ነው፡፡
በስራ መትጋት መልካም ነው ቤተሰብን መበተን ግን አደገኛ ነው፡፡

ትምህርት አስፈላጊ ነው ሳይማር ያስተማረንን ወገን የምንንቅበት ከሆነ ግን አደገኛ ነው፡፡ ቀሰው አገር መኖር ምቾት ሊኖረው ይችላል የወገንን ፍቅር በምቾት መለወጥ ግን አደገኛ ነው፡፡

ፖሊቲከኞች መቃወም ጊዜው የፈቀደው ሊሆን ይችላል አገርን መጥላት ግን አደገኛ ነው፡፡
ከዝሙት ለመራቅ ከተቃራኒ ጾታ ጋር በገደብ መኖር መልካም ነው በተቃራኒ ጾታን መጥላት ግን ተገቂ አይደለም፡፡
ገንዘብ ለማግኘት መትጋት ተገቢ ሊሆን ይችላል ያለገንዘብ አልኖርም ብሎ ግን ማሰብ አደገኛ ነው፡፡
ኑሮን በሥርዓት መምራት ተገቢ ነው ቤተሰብን እያስራቡ ገንዘብ ማጠራቀም ግን አደገኛ ነው፡፡

ሰውን ማስደሰት መልካም ነው ሰውን ሁሉ ማስደሰት ግን አደገኛ ነው፡፡
ንግግርን መቻል ጸጋ ነው ተናጋሪ ብቻ መሆን ግን አደገኛ ነው፡፡
እውነትነ መያዝ የማይገኘ እድል ነውየማይገኘ ዕድል ነው ሌላውን መቃወም ግን አደገኛ ነው፡፡
ማፍቀር መልካም ነው ማምለክ ግን አደገኛ ነው፡
ተስፋ መስጠት መልካም ነው መልሶ መቆጨትና ማዘግየት ግን አደገኛ ነው፡፡

ትዳር መልካም ነው መውረጃ ፌርማታ መፈለግ ግን አደገኛ ነው፡፡
ምንኩስና ዘመንን ለእግዚአብሔር መስጠት ነው ከነቆብ መዝለል ግን አደገኛ ነው፡፡
አንድን ነገር ከልብ መያዝ መልካም ነው ከእርሱ ውጪ ሌላ ማሰብ አለመቻል ግን አደገኛ ነው፡፡
ራስን መካድ ክርስትና ነው ራስን መጣል ግን አደገኛ ነው፡፡
ሰውን ማዳመጥና ማማከር መልካም ነው የሰውን ሚስጢር መሰርሰር ግን አደገኛ ነው፡፡
አለመቀደል መልካም ነው ካፈርኩ አይመልሰኘ ማለት ግን አደገኛ ነው፡፡"

@jahABP ነኘ

ከአደገኛው ነገር እራሳችንን እንጠብቅ እላለሁ፡፡

መልካም ምሽት ተመኘሁ
😍🙏😍😊

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →