TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1698 1.07K
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ትህትና

ትህትና የትንሽነት ምልክት አይምሰልህ፡፡ ታላቁ መስፍን ሙሴ ታላቁ ጌታ ክርስቶስ ትሁታን ነበሩ፡፡
ባለጠግነትህ ትህትናህን ሊያሳጣህ ሲሞክር ጻድቁ አብርሃምና ጻድቁ ኢዮብን ትሁታን እንደነበሩ አስብ፡፡

ስልጣንህ ልብህን ከፍ ሲያደርግብህ
"ለንጉስ ከቀን በላይ ቀን ትጨምራለህ" በማለት የተናገረውን ዳዊትን አስብ፡፡
ምንም ብትነግስ ለራስህ አንድ ቀን መስጠት አትችልምና፡፡

ደግሞም "ሁሉም ከንቱ ነው" ያለውን ሽቅርቅሩን ንጉስ ሰለሞንን አስብ፡፡ጠቢቡን ንጉሥ "ይዲዲያ" የተባለውን በማሰብ አለባበስንና እውቀትን ናቀው፡፡

ጉልበትህ ሊያስታይብህ ሲሻ ሶምሶምን አስብ፡፡ ኃይል ከኃያላን ሥልጣንህ ከሰለጠኑት እውቀትህ ካወቁት ጋር ቢነፃፀር በጣም ትንሽ ነው፡፡

በምድራዊ ነገር ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ጸጋም ልትመካ አይገባህም፡፡
ትምክህት እጄ ሀብትን ጽድቄ ጸጋን አመጣልኘ ማለት በመሆኑን ቁጥሩ ከክህደት ነው፡፡

#በጸጋ_ሳይሆን_በባለጠጋው_መመካት_ግን_ተፈቅዷል፡፡

ኃጢያትህ እየበዛ ሲመጣ የሌሎች ስህተት እየታየህ ይመጣል፡፡ ጽድቅ በውስጥህ እየተስፋፋ ሲመጣ የራስህ ደካማነት ይታይሃል፡፡

ትህትና በአደባባይ እንደ ለበስከው ነጭ ሸማ ነው ታጌጥበታለህ፡፡ ትዕቢት ግን ያዋርድሃል የማያውቅህ ሳይቀር አይቶ ይፀየፍሃል፡፡ የረጅምነት ውበቱ ዝቅ ማለት ነው፡፡
ትዕቢተኛ ስትሆን ሰዎች እንከን እንዲፈልጉብህ መንገድ ትከፍታለህ፡፡

#ትህትና_ራስን_የማወቅ_ውጤት_ነው፡፡

ራሱን በትክክል የሚያውቅ ሊታበይና በሌሎች ሊፈርድ በፍፁም አይችልም፡፡ ትህትና የሌሎችኝ ክብር ማወቅ ነው፡፡ ማክበር መከበር ነውና ሌሎችን ስናከብር ትህትና ታስከብርሃለች፡፡ ትህትና ሁልጊዜ እንደሚማሩ ሆኖ መኖር ነው፡፡

ትህትና በጠፋበት ዘመን ሁሉም አስተማሪ ይሆናል፡፡
ሁሉም ሰው ቅዱስ ነኘ በማለት ሌሎችን ያጣጥላል፡፡
ጆሮ ጠፍቶ አፍ ብቻ የበዛበት ዘመን ዘመነ ትዕቢት ነው፡፡
እገሌ ክፉ ነው ማለት በተዘዋዋሪ እኔ መልካም ነኘ ማለት ነውና ትዕቢት ነው፡፡

ትህትና የሰዎችን ትልቅ ድካም አሳንሶ ትንሽ ብርታታቸውን አጉልቶ ያሳያል፡፡ ትህትና እንዳልኖሩ ሆኖ ከሌሎች ልምድን መቅሰም ነው፡፡

ከፍ ላሉት ዝቅ ማለት ትህትና አይደለም፡፡ ከፍ ያሉትማ ግርማቸው በግድ ያሰግዳል፡፡ ትህትና ዝቅ ላሉት የምናሳየው ፍቅርና ክብር ነው፡፡
ለእግረኛ ቅድሚያ ስትሰጥ አንድ ነገር አስብ:- "መኪና ለሰው እንጂ ሰው ለመኪና አልተፈጠረም ፡፡" እውነተኛ ትህትና የልብ መሰበር ያመጣልና ለንሰሃ ያበቃል፡፡

አበባ ካልታሸ አይሸትም ፍራፍሬ ካልተጨመቀ አይጠጣም ሰውም ትሁት ካልሆነ መልኩ አይወጣም፡፡ ትህትና ያወቁትነ ያለትችት ማስተማር እንጂ አላውቅም ማለት አይደለም፡፡ እያወቁ አላውቅም ማለት ልግመት ሳያውቁ አውቃለሁ ማለት እብደት ነው፡፡ ያወቁትን በትጋት ማስተላለፍ ትሕትና ነው፡፡

የተማርከው ሌሎችን ደንቆሮ ብሎ ለመሳደብ ሳይሆን በጨለማ ላሉት ብርሃን ለማወጅ ነው፡፡
የጋን ውስጥ መብራት ከመሆን የሚያድነው ትህትና ነውና ስናውቅ ትሁት እንሁን፡፡

ፍሬ ያለው ዛፍ ዘንበል ይላል ቀና የሚሉት ፍሬ የሌላቸው ናቸው፡፡ በእውነት ካወቅህ ያላወከው ስለሚበዛብህ ትሑት ትሆናለህ፡፡ በባዶ ቤት የሚያንጎራጉር ድምፁ የሚያምር ይመስለዋል ባዶ አዳራሽም ድምፅን ያስተጋባል ጩኸት ማብዛት የባዶ ቤት ምልክት ነው፡፡

#ባዶሰው_ከቀድሞ_የከፉ_የሰባት_አጋንት_ማደሪያይ_ሆናልና_እባክህ_ባዶ_አትሁን፡፡

ትህትና የልብ ነው፡፡ የልብ ያልሆነ ትሕትና የአንገት መሰበር የጉልበት መሸበር ብቻ ነው፡፡ በልብ እየናቁ በአፍ ማክበር እርሱ ትህትና ማጣት ነው፡፡ ይልቁንም ትልቁን መንግስት መንግስተ አምላክህን እየሰበክህ ትሁት ልትሆን ይገባሃል፡፡ ሐይማኖት ማለት ትህትና ማለት ነው፡፡

ሚስኪኖችና ጦም አዳሪዎችን ኃጢያተኞችና መንገድ የጠፋባቸውን ካላዘንክላቸው ስለሃይማኖትህ አልገባህም ማለት ነው፡፡
የወደቀውን ለማንሳት ዝቅ በል ወደ ሐኪም ቤት ለማድረስ አህያህን እንደደጉ ሳምራዊ ለቀህ እግረኛ ትሆናለህ፡፡

የስድብ አምሮትህን ለመወጣት "ውሾች" ይላል ቃሉ የነቀፉ ጥማትህ "ተኩላ" ይላል ቃሉ እያልክ ከተወጣኸው ሀጢያትና በቅዱስ ነገር መበደልህ ነው፡፡ ውሻ ተኩላ የያለው ጠባያቸውን ለመግለጥ እንጂ ላንተ ስድብ ለማዳበር አይደለም፡፡

ትሀትና ተፈትኜ አልጨረስኩም ብሎ በራሱ በጣም አይመካም፡፡ ገና በፈተና ዓለም ያሉ ሰዎችንም በጣም አያመሰግንም፡፡ እባክህ ወዳጄ ትሁት ሁን፡፡

#የበላይ_የበታች_ሁሉም_ልቡ_ጎረምሳ_ሁኗልና_የሚያስተነፍስ_መዓት_ሳይመጣ_ትህትናን_ገንዘብ_እናድርግ፡፡

#ትህትናን_በማጣት_ያሳዘንከውን_አምላክህን_በብዙ_ትሩፋት_አታስደስተውም፡፡

#ትህትና_የእምነት_መጀመሪያ_ነውና፡፡

የመፅሐፉን ርዕስ ካላችሁኘ ደሞ በውስጥ መስመር አናግሩኘ፡፡

@jahABP ነኘ እንደ ትህትና ምን ደስ የሚል ነገር አለ ግን😍😍መልካሞች ሁሉ ባላችሁበት ፍቅርና አክብሮቴ ይድረሳችሁ ሰላም ሁኑልኘ፡፡

😍😍 መልካም ምሽት ተመኘሁ፡፡🙏🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →