TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1695 920
ጠዋት ነው አስታውሳለሁ ትምህርትቤታችን እንደሁል ጊዜው ድምቅ ብሎበት ነበር፡፡ የትምህርትቤታችን ዩኒፎርም ከላይ ቀይ ሹራብ ከታች ደግሞ ሰማያዊ ሱሪ ነው ከላይ ለተመለከተን የሆነ ፍክት ያለ ጽጌሬዳ አበባ ነው ምንመስለው፡፡ በተለይ ጠዋት የሰልፍ ሰዓት፡፡

እኛን ስፖርት አስተማሪን አስታወሳችኀቸው በቦክስ የእጅ ጡንቻችንን ሚማቱት(በጣም ነው ሚያመው በተለይ ለሴቶች😂😂)
እሳቸው ተማሪው ወደ ሰልፍ እንዲገባ ያገኙትን በቦክስ እየተማቱ አስተማሪዎችም ያቺ ነጭ ከሰኞ በኀላ ደግም ወደ ሽሮ ከለር የምትቀየረዋን ጋወናቸውን ለብሰው ተማሪዎችን ከየክፍሉ ያስወጣሉ፡፡ ከሁሉም የሚያስፈራው ኬሚስትሪ አስተማሪ ቲቸር ገመቹ🏃‍♂🏃‍♂ አንቴ ሚን ቲሰራለህ ቶሎ ውጣ እንጂ አንቺ ሚናባሽ ያስገለፍጥሻሊ ፈጠን ኢያልሽ ወዴ ሰልፉ እያለ....እሺ ሚዋከበው ማትስ አስተማሪ ቲቸር ይመርስ
ዝምተኘነቷ እና እርጋታዋ ሚስበን እሷን ብቻ እንድንሰማ እሷን ስናይ ብቻ ሮጥ ሮጥ ምንለዋ ቲቸር ቦንቱ😍

ከሁሉም ደግሞ ሁሉም ሰው ሚደነብረው ፍንዳታ ሚባሉት እራሱ መጣ መጣ ተባብለው ተሽቀዳድመው ሰልፍ ቦታ ላይ ሚገኙት
( እኔ እንኳን አልፈራውም ነበር ለምን እንደሆነ አይገባኘም) በእርግጥ ምንም ነገር አላጠፋም ነበር ለዛ ይሆናል🤷‍♂ ብቻ የትምህርትቤታችን ጠቅላያችን ገዢ አሰናባች የእናቶች ለቅሶ ግድ ማይሰጠው ርዕሰ-መምህራችን #ሰማኸኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

ብቻ የዛኑ ቀን ሁሉንም ተማሪዎች አብዛኛውን ሰብስበው ሰልፍ ላይ ቆምን ዛሬ ለምን እንዲ ሁሉንም ከክፍል ከሜዳ እንደሰበሰቡት እንጃ እየለ ተማሪው ይንሾካሾካል፡፡

ማይክ መጣ ሙከራ አንድ ሁለት ሶስት ተባለ ማይክ የያዘው ሰውዬ ተሽቆጥቁጦ ለርዕሰ መምህራችን ሰጠው እሱ ሲያወራ ማነው ሌላ ወሬ ሚያወራ......ዝም ለምን በተማሪ ፊት ሚማታው ምት😱😱 አስተማሪዎቹም ዩኒትሊደሮችም ከሱ ሙገሳን ለማግኘት በፊቱ ተማሪን ይኮረኩማሉ....ተማሪ ላዬ ይጮኻሉ...

ንግግሩን ጀመረ ስለጥያቄና መልስ ውድድር ነው ወይ ጉዴ አልኩኘ ትላንት ነው ውድድር የጨረስነው እኔም ክፍሌ 7A ወክዬ ተወዳድሬያለሁ ውጤተት አልተነገረንም ነበር ግን እንዲ በዚ ሁሉ ተማሪ ፊት ግን ያደርጉታለ ብዬ አላሰብኩም🤦‍♂🤦‍♂፡፡


እና ተናግሮ ተናግሮ ከሰባተኛ 7 ክፍል አንድኛ የወጣው...የወጣችው.....😳😳😳😳
#ዓባይ_አንዱአለም አላለም አስተማሪዎቼም የክፍለ ጓደኞቼም ምን እነንደነካቸው እግዜር ይወቅ እሱ ሲያወራ ቃል ማይወጣቸው አብይ ነው አብይ ነው አሉ እሱም እንደማፈር ብሎ አብይ እዱአለም ብሎ አስተካከለ ምን ውስጥ ልግባ 🤦‍♂🤦‍♂🙈🙈🙈🙊🙊🙊አፈርኩ እንዴት ብዬ ወጥቼ ነው ሽልማቴን ምቀበለው በጣም ብዙ ተማሪ ነው፡፡ ጓደኞቼም ሌሎች ሚያቁኘም እያደፋፋሩ ሔድኩኘ ሽልማቴን እና የምስክር ወረቀቴን ተቀበልኩ፡፡

ከጠዋት ቤት እስክሔድ የምስከር ወረቀቴን አላየሁትም የክላስ ተማሪዎች ሌላ ክፍሎችን እያበሸቁበት እኔ ጋር አልዋለም ነበር ስቀበለው አዲስ የነበረው ወረቀት ከሆነ ሱቅ ለዳቦ ተብሎ እንደተሰጠ ብጣሽ ወረቀት ሳስቶ እና ተጨማዶ ነበር፡፡
አሁንም የምስክር ወረቀቱ ዓባይ አንዱአለም ነው ሚለው፡፡😂😂😂ትዝታ ነው ብዬ

ይህ ሁሉ ሲሆን እኔ እሷን ነበር ምፈልጋት ከትርምሱ መሃል አየኀት ወዳለችበት ከሰው ጋር እየተጋጨው እንደምንም ደረስኩ ወደ እሷ ጠጋ ብዬ እንዲህ አልኳት ይህን ሽልማት ያገኘሁት አንቺ እዚህ ውድድር ውስጥ ስላልነበርሽ ነው አንቺ ብትኖሪ ማርያምን ሁለተኛ ነበር ምወጣው ይህ ያንቺ ሽልማት ነው አልኳት፡፡ ዝም በል ስለበለጥካቸው ነው ያሸነፍከው አለችኘ በማፈር፡፡አልወዳደርም ስትል አንተ አሸንፍ ብላ የሰጠችኘ እስኪመስለኘ ድረስ ነበር የገረመኘ
ለምን ብዬም ሞግቻታለሁ ድርቅ አለችብኘ እንጂ፡፡


ይኸው የዛሬ ዘጠኘ አመት ያገኘኀት ምርጧ እህቴቴቴ ውዴ የኔ #መቅደስ_ሲሳይ ዲግሪዋን ጭናለች እንኳን ደስ አለሽ መቅዲዬ ይህ ላንቺ ይገባሻል ከዚህም በላይ ነው የሚገባሽ ለጥቂት ያጣሽውን😡😡 ሜዳሊያ በማስተርሱ እንደምታመጪ😊💪💪😍እርግጠኛ ነኘ አንቺ ምርጥ ማርያምን ደስ ብሎኛል ጋዎንሽን ለብሰሽ እንደዛ ሱክ ሱክ ስትይእንዴት ደስ እንዳለኘ ነፍሴ እንዴት ሀሴት እንዳደረገች አታውቂም ከልብ ነበር ደስ ያለኘ፡፡

የጥንካሬ ምሳሌዋ #መቅደስ_ሲሳይ በድጋሚ እንኳን ደስ አለሽ😍😍😘😘😘😘😘🔥🔥🔥

#ምግቦቹ ደግሞ😋😋😋😋እጃቸው ይባረክ

#እግዚአብሔር_አምላክ_ከእነ_እናቱ_ድንግል_ማርያም_ጋር_የተመሰገነ_ይሁን፡፡

👏👏👏 ur bro AB ሁሌም ከጎንሽ💪💪💪
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →