TGViewer
Phenomenal pictures & graphic design Phenomenal pictures & graphic design @abpgd · 1.08K subscribers
Post #1692 1.02K
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ማምሻ

#ሴቶች ይህን የአሌክስ አብርሃም ፅሁፍ አንብቡልኘ......

አስታውሳለሁ አሌክስ አብርሃምን እወደዋለሁ ብዬ ነበር ይህንን መፅሐፍ የጀመርኩት፡፡

ይኸው ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር የምጣላበትን ቀደም ብዬ መፅሐፉ ከመውጣቱ በፊት እራሴ የፃፍኩትን ፅሁፍ ማንበብ ይቻላል...

አሌክሶ ደግሞ ማምሻ በምትባል ሴት ልጅ መስሎ ሌላ ደግሞ ሎዛ የምትባል ቅመም ጨምሮበት የማህበረሰባችንን ችግር እንዲህ ያስቃኘናል ......

ሴት ልጆች አላችሁ ይህን ፅሁፍ አንብባችሁትስ ይሆን🤔🤔 አው እናንተን ይመለከታል

#ሎዛ በቁጭት እንደዚህ ትላለች(ፍልስፍና ነው ያጠናችው) .....

"በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 'ሴትነትና ቁንጅና' የሚባል የእስር ፍርግርግታችን እያርዋብን ተሟሙቀን የወንዶች ጭብጨባና አድናቆት እየጠበቅን እንድንኖር ሁነናል፡፡
ሁሉም ሰንሰለቱን ፈቶ አይታይም....እንደውም አንዳንዱ እስራት ለታሳሪው ጭምር አይታይም፡፡

ማህበረሰቡ አንዲት ሴት "የብረት መዝጊያ የሚሆን አማች የምታመጣ እንጂ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም! ስለዚህ የእነሱን የምኞት በር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት አንዲት ሴት ዓይኗንም አእምሮዋንም ሳይሆን #እግሯን_እንድትከፍት ከህፃንነቷ ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል"

"እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያው ዓላማው መራመድ ነው ለሴት ልጅ ግን ከመራመድ በላይ እግር ውበት እንደሆነ እንድታስብ በሥነ-ፅሁፉ በፊልሙ *በዘፈኑ በእምሮዋ ውስጥ ሲታጨቅባት ኖሯል *እየታጨቀባትም ነው፡፡
ከመራመዷ በላይ አረማመዷን እና የእግሯን ውበት እንድታስብ ስትሰበክ ኖራለች፡፡

ለዚያም ነው ከፊታቸው የተነጠፈውን እሾህም ይሁን ጠጠር ረግጠውና ዋጋ ከፍለው ወዳሰቡበት ከሚራመዱት ሴቶች ይልቅ ከየትም ባገኟት ሳንቲም በየውበት ሳሎኑ ተጎልተው እግራቸውን የጥፍር ቀለም ሲያስቀቡና ተረከዛቸውን ሲያስፈገፍጉ የሚውሉ ዘመነኞች የሚበዙት፡፡ እግራቸው ከለሰለሰ በኀላ አዝሎ የኒያሻግር ወንድ ሲጠብቁ ቁጭ ብለው ይኖራሉ፡፡

እጅ የተፈጠረበት የመጀመሪያው አላማው መስራት ነው፡፡ ብዙ የፋሽንና እና የዘመናዊውን የውበት ሚዛን የሚደፉ 'ዘመናዊ' ሴቶች እጃቸው ከሚበላሽ ስማቸውም ሕይወታቸውም ቢበላሽና እና እጃቸውጠእንደለሰለሰ ቢኖር ይመርጣሉ፡፡
በልስላሴ ሳይሆን በንፅህና እራስን ችሎ በመቆም እንጨባበጥ ከተባለ ማን ናት ደፍራ እጇን የምትዘረጋ?!

ለብዙሃን ወንዶች ጠንካራ የሴት እጅ አገር ያቆመ ሳይሆንጨሴትነትነ የገፉ መስሎ ነው የሚታያቸው፡፡ ለዚያ ነው በስራ ስለደደረ የሴት መዳፍ ዘፋኙም መዝፈን ገጣሚውመ መግጠም የማይወደው፡፡ ድንጋይ ፈልፍሎ እምነበረደ ጠርቦ ውብ የእጅ ጣት ያላት የሴት ሐውልት የሚያሾመው ቀራጺ እጅ ግን ተመልከተው በስራጨየጎለደፈ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡

ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝብ ሴት በሆነበት ሀገር ሴትች ወንድ በጭናቸው መሀል ካላፈ የሚመስላቸው እጃቸውን አስውበው መደርደሪያ ላይ እንዲያስቀም ጡት በማድረግ ለውጥ ጠብ አይልም እንዲሰሩ.. ማደፋፈር.. እጅ... ወደተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማ እንዲመለስ መሰበክ አለበት!! "

አሌክስ አብርሃም፡- ከዕለታት ግማሽ ቀን

ሴቶች ተጋበዙልኘ.......

@jahABP ነኘ

እኔም እላለሁ ገላዋን አይቶ የመጣ ገላውን አይቶ ይሔዳል እና እህቴ እባክሽን ከዘመንኛ አስተሳሰብ አምልጪ አንቺ ሁሉንም ማድረግ ትቺያለሽ ቁጭ ብለሽ እሱን አትጠብቂ፡፡
በዚ ጊዜ የሴትነት ክብር በጣም የዘቀጠ ሆኖ እያገኘሁት ነው የሰሞንኛ መነጋገሪያዎችንም ጨምሮ ባለፈውም የጋበዝኩት የኀይሌ ሩትስ ዘፈኝ ላይ "ማንነትሽን ገንዘብ ላይተካው ለምን ማንም ክብርሽን ይንካው ይላል" እና እባካችሁን እላለሁ 😔😔😔😔😔

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

፡፡ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም እያሰብን እንራመድ፡፡
እላለሁ

መልካም ምሽት መልካም አዳር

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
More from @abpgd
  1. Apr 21, 2025#የሞት_ሞት "ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል ሰለሞን እጠይቀው ነበር በተገናኝን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሆን?" ነፍሳቸውን ይማረውና ክቡር ዶ/ር…
  2. Sep 14, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  3. Sep 13, 2024#PHENOMENAL_picture #እንኳን_አደረሳቹ #መልካም_በዓል #አቤል_የሀገር_ባህል_አልባሳት ይዘዙን በየትኛውም ሀገር እንልካለን 📸 @a…
  4. Mar 24, 2024#PHENOMENAL_picture @abiy_yemaryam_lej #መልካም_እለተሰንበት_ይሁንልን #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ #መድኃኒዓለም_አባቴ #…
  5. Mar 2, 2024AB PHOTOGRAPHY ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት እምየ ምንሊክ ጀ…
  6. Feb 5, 2024Phenomenal picture ደረሰ ደረሰ ደረሰ " ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →