TGViewer
Channel ✦ Verified Channel
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

@ethpress

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Subscribers
24.8K
Photos
41.4K
Videos
346
Links
5.8K

Showing posts older than #46715 · Back to latest

Older Posts 6 shown
Post #46714 2.98K
ቱሪዝም- አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ቱሪዝምን አሰመልክቶ ከNBC ጋር ባደረጉት ቆይታ ካነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች‼️

👉 ለቱሪዝም ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት መነሾ ራዕያችን ነው

👉 ራዕያችን የበለጸገች የተለወጠች የተከበረችና የተወደደች ሀገር ሰርተን ለልጆቻችን ማስረከብ ነው፣

👉 በዚህ ዓመት ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ጎብኝ ኢትዮጵያን ጎብኝቷል፤ ከ5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል

👉 በቀድሞ ጊዜ በነበረው የትርክት ችግር በቱሪዝም ዘርፉ አለን ከማለት ያለፈ ሥራ አልነበረም፣

👉 ቅርሶቻችን እንደ ዕዳ ከመታየት ወጥተው ታድሰው ተጠግነው ውብ ሆነው ወጥተው ምንዳ ሆነው ሀብት እያስገኙ

👉 ቅርስ የምናስመልስ የምንጠብቅ እንጅ ቅርስ የምናፈርስ አይደለንም

👉 ቱሪዝምን ከአምስቱ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች በመመደብ በመደመር ዕሳቤ በትኩረት እየሠራበት ነው፣

👉 ባለፉት 7 ዓመታት ከዚህ ቀደም የተዘረፉ ከ35 በላይ የኢትዮጵያ ቅርሶች ተመልሰዋል

👉 እንደ ሀገር ቅርስ ከመመለስ በተጨማሪ ቅርስ በማደስ የሚጎሉትን ደግሞ ገንብተን ለአገልግሎት አብቅተናል፣

👉 ቱሪዝም ከብዘሃ የኢኮኖሚ ሴክተሮች አንዱ ተደርጎ ተወስዶ እየተሰራ ነው

👉 በዓለም ላይ በቱሪዝም ሴክተር የሚንቀሳቀሰው ሀብት መጠን በጣም ከፍተኛ ነው

👉 ለዘመናት ኢትዮጵያ አያሌ ጸጋዎች እንዳሏት እናምናለን እንናገራለን በዚህም እንኮራለን፣

👉 ቱሪዝም ላይ ኢንቨስት ማድረግ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ያለውን ሃብት ለመቋደስ ያስችላል

👉 ኢትዮጵያ በርካታ የቱሪዝም መስህቦች አሏት እሱን የሚያውቁ ፣ የሚያዩና የሚያሳውቁ ውስኖች ናቸው

#LandOfOrigins #Medemer #ገበታለሀገር #ገበታለትውልድ #TravelEthiopia #EcoTourism
  • ❤ 2
  • 🔥 1
Post #46713 2.67K
Post #46702 3.17K
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ የተመረቀው የእንጦጦ-ቀበና የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በፎቶ
  • ❤ 16
  • 😁 3
Post #46695 3.2K
16 A+ ያስመዝገበው የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የዓመቱ ኮኮብ ዘለቀ መንግስቴ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት ካሰመረቃቸው ከአንድ ሺህ 817 ተማሪዎችን መካከል የሰርቬይ ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ተማሪው ዘለቀ መንግስቴ የዓመቱ ኮከብ ተማሪ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን አንድ ሺህ 817 ተማሪዎችን በአደዋ ድል መታሰቢያ አስመርቋል።

ተመራቂ ዘለቀ መንግስቴ በዩኒቨርሲቲ ቆይታው ከወሰዳቸው 58 ኮርሶች 16 A+ በማስመዝገብ የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

​ዘለቀ ባለትዳና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን፤ ለስኬቱ የቤተሰቦቹ ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሶ፤ በተለይም የባለቤቱ የዕለት ተዕለት ድጋፍ ለውጤቱ መሳካት ትልቅ እገዛ ማድረጉን ገልጿል፡፡

በየዩኒቨርሲቲ ቆይታው ከአካዳሚክ ትምህርት ባለፈ ብዙ ጥሩ ነገሮችን መማሩን የሚናገረው ዘለቀ፤ በቀጣይም በተማረበት የሞያ ዘርፍ ሀገሩን በታማኝነት ለማገልገል መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ንጉሥ ታደሰ (ዶ/ር) በምረቃው ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ትምህርት የህይወት ዘመን ጉዞ መሆኑን በመገንዘብ ምሩቃን ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም ሀገራቸውን እንዲሁም ህዝባቸውን በታታሪነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።

ዩኒቨርሲቲው በትምህርት፣ በአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች፣ በጥናትና ምርምር በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች የሀገሪቱን የፐብሊክ ሴክተር ተቋማዊ አቅም ግንባታ እያጠናከረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በአማን ረሺድ

#ጋዜጣ_ፕላስ #ፕብሊክየኒቨርሲቲ #ተማሪምርቃት #ኢትዮጵያ #EthiopiaDelivers #gazetteplus #graduation
  • ❤ 6
  • 👍 5
Post #46691 2.44K
አበባየሁ ደሳለኝ ትባላለች፤ የሦስተኛ ዲግሪ ተመራቂ ከልጇ ጋር
+++++++++++

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ከሚያስመርቃቸው 6ሺህ 417 ተማሪዎች መካከል 2 ሺህ 646 ሴቶች ናቸው። 377 የሶስተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች መሆናቸው በምረቃው ስነስርዓት ላይ ተገልጿል።
  • ❤ 3
Older posts →
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →