Post #46112
2.08K

በአዘርባጃን ባደረግኩት የመጀመሪያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ላደረጉልኝ ሞቅ ያለ እና የተከበረ አቀባበል ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአቪዬሽን ዘርፍ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በነፃ የንግድ ቀጣናዎች፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በአዘርባጃን አቻው መካከል በተደረጉ የኢኮኖሚ ትብብሮች ላይ በመመስረት አጋርነታችን በየጊዜው እያደገ መጥቷል። እነዚህ የትብብር ዘርፎች ለሁለትዮሽ ግንኙነታችን መጠናከር መሠረት የጣሉ ሲሆን፣ ዛሬ ባደረግነው ጥልቅ ውይይትም ግንኙነታችንንና ትብብራችንን ይበልጥ ለማጠናከር እና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ተስማምተናል።
በዛሬው ዕለትም በመከላከያና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነዶች ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተናል።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

- ❤ 5