TGViewer
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ @ethpress · 24.8K subscribers
Post #46769 5.05K
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያን ስራ አሰጀመሩ
++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ የደብረ ማርቆስና የአካባቢው ሕዝብ ለዓመታት በጉጉት ሲጠብቀው የነበረውና ለ30 ዓመታት ያህል ተቋርጦ የነበረው ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት የአውሮፕላን ማረፊያ፤ በዘመናዊ መልክ ተሻሽሎና ደረጃው ከፍ ብሎ ተገንብቶ ዛሬ መመረቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

በ2,400 ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር ስፋት ላይ የተገነባው እንደ Q400 እና B737 ያሉ ግዙፍ የሕዝብና የጭነት አውሮፕላኖችን ማሳረፍ የሚያስችል ከፍተኛ ዐቅምም ፈጥሯል።

ይህ አውሮፕላን ማረፊያ ሥራ መጀመሩ የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት ለአካባቢው እና ለመላው ሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል።

ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር፤ የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስና የጀመርናቸውን ሜጋ ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለምርቃት ለማብቃት ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየን እንቀጥላለን ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

#NationalDialogue #ሀገራዊምክክር #ኤርፖርት #airport Ethiopian Airlines
  • ❤ 4
More from @ethpress
  1. Oct 3, 2026የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙና የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ም…
  2. Oct 3, 2026photo post
  3. Oct 3, 2026photo post
  4. Oct 3, 2026በሆረ አርሰዴ ታዳሚዎች የደመቀችው ቢሾፍቱ ከተማ ++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- በነገው ዕለት የሚከበረውን የሆረ አርሰዲየኢሬቻ በዓል ለመ…
Threads Profile ViewerView any public Threads profile without an account.Open ThreadLook →Writing with AI? Make it sound human.Metric37 rewrites AI drafts so they read naturally. Free AI detector, 1,500 words free.Try Metric37 →